ወላይታ ድቻ ጃኮ አረፋት እና አምረላህ ደልታታን አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ወላይታ ድቻ የሁለት ተጫዋቾችን ፊርማ ማጠናቀቅ ችሏል፡፡ ጃኮ አራፋት እና አምራላ ደልታታም ለክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በመጀመሪው አመት ነጥረው ከወጡ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው እና ለሀዋሳ ከተማ 12 የሊግ ግቦች በማስቆጠር ድንቅ አመት ያሳለፈው የቀድሞው የአንዚ ማካቻካላ እና ሲኤፍ ሞናና አጥቂ ስሙ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክለቦች እና የእስራኤል ፕሪምየር ሊግ ክለቡ የሆነው ሀፖኤል አክሬ ጋር ቢያያዝም ለእረፍት ካመራበት ሀገሩ በመምጣት በቃል ደረጃ ተስማምቶበት የነበረው ወላይታ ድቻን በአንድ አመት ውል መቀላቀሉ ታውቋል፡፡

ሌላኛው የወላይታ ድቻ ፈራሚ የሆነው አምረላ ደልታታ ነው፡፡ በሀዲያ ሆሳዕና ጋር ሁለት የውድድር ዘመናትን ማሳለፍ የቻለው የቀኝ መስመር አማካዩ ሀዲያ ሆሳዕና ምንም እንኳን በዘንድሮው አመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ባይቀላቀልም መልካም የውድድር አመት ማሳለፍ ችሏል፡፡

ወላይታ ድቻ በዝውውር መስኮቱ ሁለቱን ጨምሮ በአጠቃላይ 9 ተጫዋቾችን ማስፈረም ችሏል፡፡

ቴዎድሮስ ታከለ

ቴዎድሮስ ታከለ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ቴዎድሮስ ታከለ ነኝ

ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነውሊያገኙኝይችላሉ
ቴዎድሮስ ታከለ

ቴዎድሮስ ታከለ

ይህንን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ቴዎድሮስ ታከለ ነኝ ከፎቶው በታች ያለው የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ

One thought on “ወላይታ ድቻ ጃኮ አረፋት እና አምረላህ ደልታታን አስፈርሟል

  • August 10, 2017 at 4:42 pm
    Permalink

    esay ahun des alegn, betam tiru ena wutetam ziwuwur new tilk astewatso yemiberekitu techewachoch nachew betelay Arafat Jako.

    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *