ጅማ ተጨማሪ 3 ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ጅማ አባ ጅፋር በዛሬው ዕለት ያስፈረማቸው ተጫዋቾች ቁጥር 5 ደርሷል። ከፋሲል ጋር የተለያዩ ሶስት ተጫዋቾችም ክለቡን ተቀላቅለዋል።

ፋሲል ከነማ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲገባ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት እና በሊጉም ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከአፄዎቹ ጋር የቆዩት ተከላካዩ ከድር ኸይረዲን፣ አማካዩ ኄኖክ ገምተሳ እና ሌላው አማካይ ይስሀቅ መኩርያ ወደ ጅማ አባጅፋር ያደረጉትን ዘውውር አጠናቀዋል። 

ሶስቱም ተጫዋቾች የሁለት ዓመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን በአጠቃላይ ካስፈረማቸው አምስት ተጫዋቾች መካከል አራቱ ፋሲልን የለቀቁ መሆናቸው አስገራሚ ሆኗል። 

ጅማ ከሶስቱ ፈራሚዎች ቀደም ብሎ ኤርሚያስ ኃይሉ እና መስዑድ መሐመድን ማስፈረሙ የሚታወስ ነው።