ኢትዮጵያ ቡና ረዳት አሰልጣኝ ሾሟል

የአሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ ረዳቶችን በአዲስ መልክ በማዋቀር ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ ቡና ሲሳይ ከበደን ምክትል አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙ ታውቋል። አስራት አባተ እና ኢስማኤል አቡበከርን ጨምሮ በርካታ አሰልጣኞች ለክለቡ ምክትል አሰልጣኝነት ታጭተው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም ሲሳይ ከበደ በአንድ ዓመት ውል የዲዲዬ ጎሜስ ረዳት ሆነው ተሹመዋል።

ሲሳይ ከበደ የአሰልጣኝነት ህይወታቸው አብዛኛውን ጊዜ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ረዳት አሰልጣኝነት ያሳለፉ ሲሆን በ2009 አጋማሽ ጸጋዬ ኪዳነማርያምን ተክተው በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ሰርተዋል። አሰልጣኙ በ2010 ታዳጊዎችን ሲያሰለጥኑም ቆይተዋል።

የዲዲዬ ጎሜስ ረዳት የነበሩት መሐመድ ኢብራሒም እና ተክለወልድ ደስታ እንዲሁም የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ውብሸት ደሳለኝ ከክለቡ ጋር የተለያዩ ሲሆን የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ፀጋዘዓብ አስገዶም አዲሱ የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።