ከፍተኛ ሊግ | ሀዲያ ሆሳዕና ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾች አስፈርሟል

የቀድሞ አሰልጣኙ ግርማ ታደሰን በመሾም ለ2011 የከፍተኛ ሊግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ በመግባት ስድስት ተጫዋቾችን በአንድ ዓመት የውል ስምምነት አስፈርሟል።

በምድብ ለ የሀዲያ ሆሳዕና ተፎካካሪ በሆነው ሀላባ ከተማ ላይ መልካም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የቆዩት ተከላካዩ አዩብ በቀታ፣ የመስመር ተጫዋቸቹ ተመስገን ይልማ እና ስንታየሁ አሸብር ወደ ሆሳዕና ያመሩ ተጫዋቾች ሲሆኑ ሌላው የቀድሞ የሀላባ ተከላካይና የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ ቡና ያሳለፈው ትዕግስቱ አበራም ወደ ሆሳዕና አምርቷል። ነጌሌ ከተማን ለቆ ያለፉት ሁለት የውድድር ዓመታትን በወላይታ ድቻ ያሳለፈው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ዳግም በቀለ እንዲሁም የሀምበሪቾው ፀጋሰው ድማሙ ሌሎች የሀዲያ ሆሳዕና አዲስ ፈራሚ ናቸው።