ኢትዮጵያ ቡና የነገውን ጨዋታ አዳማ ላይ እንደማያደርግ አስታወቀ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በትላንትናው ዕለት ሳይካሄድ የቀረው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ በነገው ዕለት በአዳማ አበበ ቢቂላ በዝግ እንዲካሄድ መወሰኑ የሚታወስ ነው።

በውሳኔው ዙርያ ኢትዮጵያ ቡና ተቃውሞውን የገለፀ ሲሆን የፌዴሬሽኑን ውሳኔ እንደማይቀበል በመግለፅ በአሁኑ ሰዓት በዋቢ ሸበሌ ሆቴል መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። የክለቡ ፕሬዝዳንት መ/አለቃ ፍቃደ ማሞም ነገ ጨዋታ እንደማያደርጉ በመግለጫው አስታውቀዋል።

“ደጋግሜ የምነግራችሁ ኢትዮጵያ ቡና ነገ ወደ አዳማ በመሄድ የሚያደርገው ጨዋታ እንደማይኖር ነው። ፌዴሬሽኑ ይህን ውሳኔያችንን የማይቀበል ከሆነ ለክለቡ ህልውና ስንል ፊፋ እና ካስ ይዘነው እንሄዳለን። ” ሲሉ መቶ አለቃ ፈቃደ ተናግረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: