የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች የቅሬታ ደብዳቤያቸውን ለፌዴሬሽኑ አስገቡ

የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች ክለቡ “በተደጋጋሚ ያልተከፈ ወርኃዊ ደሞዛችንን እንዲከፍለን ብጠይቅም ምላሽ አጥተናል።” በማለት ለእግርኳሱ የበላይ አካል የቅሬታ ደብዳቤ አስገብተዋል።

ከሦስት እስከ አራት ወር ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የሚገልፁት ተጫዋቾቹ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ምንም ዓይነት ምላሽ ክለቡ ሊሰጣቸው እንዳልቻለ ተናግረዋል። ፌዴሬሽኑም ቅሬታችንን ተመልክቶ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው አስራ ስድስት ተጫዋቾች ዛሬ በደብዳቤ ቅሬታቸውን ገለፀዋል።

ያስገቡትን ደብዳቤ ተከትሎ የፌዴሬሽኑ የፍትህ አካላት ምላሽ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡