ኄኖክ መርሹ ቢጫ ለባሾቹን ተቀላቅሏል

የዘጠኝ ተጫዋቾች ዝውውር ያጠናቀቁት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ኄኖክ መርሹን ከደደቢት አስፈርመዋል።

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ወጥቶ የደደቢትን ታዳጊ ቡድን በመቀላቀል ላለፉት 3 ዓመታት በዋናው ቡድን ቆይታ ያደረገው ተጫዋቹ ባለፈው ውድድር ዓመት በቡድኑ ቋሚ ተሰላፊ የነበረ ሲሆን ከድሬዳዋ ከተማ በነበረው ጨዋታ ላይም ከርቀት ግሩም ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

የወልዋሎ አስረኛ ፈራሚ የሆነው የግራ መስመር ተከላካዩ በወልዋሎ ለቋሚ ተሰላፊነት ከሌላኛው አዲስ ፈራሚ ሳሙኤል ዮሐንስ ጋር የሚፎካከር ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡

error: