መቐለ 70 እንደርታ የተከላካይ ክፍል ተጫዋች አስፈረመ

በትናንትናው ዕለት ኦኪኪ ኦፎላቢን በእጃቸው ያስገቡት ምዓም አናብስት ዛሬ ደግሞ ተስፋዬ መላኩን አስፈርመዋል።

ባለፈው ዓመት ሲቸገሩበት የነበረውን ጠባብ የተከላካይ ክፍል አማራጭ ለማስፋት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ቻምፒዮኖቹ ቀደም ብለው ታፈሠ ሰርካን ማስፈረማቸው ሲታወስ አሁን ደግሞ ተስፋዬ መላኩን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል። በግራ እና መሐል ተከላካይነት መጫወት የሚችለው ይህ የቀድሞ ወላይታ ድቻ እና ኤሌክትሪክ ተጫዋች የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በጅማ አባ ጅፋር አሳልፏል።

በቀጣይ ቀናት በቡድኑ ወሳኝ ቦታዎች ላይ ተጨማሪ ዝውውሮች ይፈፅማሉ ተብለው የሚጠበቁት መቐለ 70 እንደርታዎች የነባር ተጫዋቾች ውል እንደሚያራዝሙም ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: