ያሬድ ባዬ ከሩዋንዳው ጨዋታ ውጪ ሆነ

ባህር ዳር ላይ ልምምዳቸውን እያከናወኑ የሚገኙት ዋሊያዎቹ ያሬድ ባዬን ከስብስባቸው ውጪ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ወጥ ብቃት በማሳየት ከሊጉ ምርጥ ተከላካዮች አንዱ የነበረው ያሬድ ባዬ ለሩዋንዳው ጨዋታ በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጥሪ ቢቀርብለትም በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ ሆኗል። ከክለቡ ፋሲል ከነማ ጋር የቅድመ ውድድር ዝግጅት ሲያደርግ ጉልበቱ ላይ ጉዳት ያጋጠመው ያሬድ በቡድኑ የህክምና ክፍል ለጨዋታው እንደማይደርስ እንደተነገረው ታውቋል።

ልምምዳቸውን ዛሬ 4 ሰዓት ያደረጉት ዋሊያዎቹ ትላንት መጠነኛ ጉዳት ያስተናገደው አስቻለው ታመነን ማግኘት የቻሉ ሲሆን በተጨማሪም ከትላንት በስትያ መጠነኛ ጉዳት ያስተናገደው ግብ ጠባቂው ጀማል ጣሰው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ዋሊያዎቹ ነገ ረፋድ 4 ሰዓት ዩጋንዳን በወዳጅነት ጨዋታ እሁድ በሚገጥሙበት ባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዳቸውን እንደሚያደርጉ ታውቋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: