የካፍ ልዑካን ቡድን የወልዲያ ስታዲየምን ጎበኘ

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የልዑካን ቡድን አባላት በወልዲያ ከተማ በመገኘት የመሐመድ ሁሴን ዓሊ አል አሙዲ ስታዲየምን ጎበኝተዋል።

ቡድኑ ጉብኝት ያካሄደው ስታዲየሙ የካፍን ጨዋታ የሚያስተናግድ መሆን አለመሆኑን እና የዓለም አቀፉን የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) መለኪያ መስፈርቶች ማሟላት አለማሟላቱን ለመገምገም ነው።

በጉብኝቱ ላይ የሜድሮክ ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ አረጋ ይርዳው እና የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ዘሪሁን ቀቀቦ ተገኝተው ስለ ስታዲየሙ ይዘት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጉብኙቱን ተከትሎ ካፍ የደረሰበትን ማጠቃለያ አስተያየት ወይም ውሳኔ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ከወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ