ባህር ዳር ከተማ ከአሞሌ ጋር ስምምነት ተፈራረመ

ባህር ዳር ከተማ ከአሞሌ ጋር የትኬት አሻሻጭ ሥርዓት ጋር የተገናኘ ስምምነት ተፈራረመ።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና ሰበታ ከተማ ጋር ስምምነት ፈፅሞ ሥራዎችን እየሠራ የሚገኘው አሞሌ ዛሬ ከሰዓት ከባህ ዳር ከተማ ክለብ ጋር ለመስራት ተስማምቷል። የጣና ሞገዶቹ በሜዳቸው የሚያደርጓቸው ጨዋታዎችን በአግባቡ ትኬት ለመሸጥ የተስማሙት ሁለቱ አካላት ውላቸው እስከ ዓመቱ መጨረሻ እንደሚዘልቅም ታውቋል።

በአሞሌ በኩል የሚዘረጋው የትኬት አሻሻጭ ሥርዓት ቡድኑ ባህር ዳር ከተማ የፊታችን ረቡዕ ከአዳማ ከተማ ከሚያደርገው ጨዋታ ጀምሮ በሥራ ላይ እንደሚውል ተጠቁሟል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: