መቐለ 70 እንደርታ የሦስት ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም ተስማምቷል

ምዓም አናብስት የሦስት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸው ውል ለማራዘም ተስማምተዋል።

በትናንትናው ዕለት ወደ እንቅስቃሴ ገብተው የአምስት ተጫዋቾች ውል ያራዘሙት 70 እንደርታዎቹ አሁን ደግሞ የሥዩም ተስፋዬ፣ ዮናስ ገረመው እና አሚን ነስሩን ውል ለተጨማሪ ዓመታት ለማራዘም መስማማታቸውን  ለማወቅ ተችሏል። በቃል ደረጃ ከቡድኑ ጋር ለመቀጠል የተስማሙት እና በቀጣይ ቀናት ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብለው የሚጠበቁት እነዚህ ተጫዋቾች ቡድኑ ዋንጫ ያነሳበትን ዓመት ጨምሮ ላለፉት ሁለት ዓመታት ክለቡን በቋሚነት ማገልገላቸው ይታወሳል።

ከተስፋዩ በቀለ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል እና አልሃሰን ካሉሻ ውጭ ውል ያለው ተጫዋች ያልነበራቸው መቐለዎች ከትናንት ጀምሮ ውል የማራዘም ሥራ ውስጥ የገቡ ሲሆን በተጨማሪም በርካታ አዳዲስ ፊቶች ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል በሰፊው ወደ እንቅስቃሴ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: