ሀዋሳ ከተማ ዝውውሩን ተቀላቅሏል

ሀዋሳ ከተማ ግብ ጠባቂው ሶሆሆ ሜንሳ እና ተከላካዩን ዘነበ ከድርን ለማስፈረም ተስማማ፡፡

የጋቦኑን ሞናና ክለብ ለቆ በ2009 ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኃላ ሀዋሳ ከተማን ተቀላቅሎ መጫወት የጀመረው ቶጓዊው ግብ ጠባቂ ሶሆሆ ሜንሳ በሀዋሳ ከተማ ድንቅ ሶስት አመታትን ካሳለፈ በኃላ ነበረ ወደ ወልቂጤ ከተማ በተሰረዘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር አመት ተዘዋውሮ በመጫወት ያሳለፈው ተጫዋቹ በድጋሚ በአንድ ዓመት ውል በድጋሚ ሀዋሳን ለመቀላቀል ተስማምቷል፡፡

ሌላኛው ሀዋሳን የተቀላቀለ ተጫዋች ዘነበ ከድር ነው፡፡ ይህ የቀድሞው ገላን ከተማ እና ነገሌ ቦረና የመስመር ተከላካይ በፕሪምየር ሊጉ እና በከፍተኛ ሊጉ ደቡብ ፖሊስን ለሁለት የውድድር ዓመታት ካገለገለ በኃላ ለሀይቆቹ በሁለት ዓመት ውል ለመፈረም ተስማምቷል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: