የቡድን ግንባታ እና ሒደቱን በተመለከተ ለሀገራችን አሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል

አሰልጣኞች ቡድን በምን አይነት መልኩ ማዋቀር፣ መገንባት፣ ማዋሀድ እና የቡድን ስብጥርን እንደሚፈጥሩ የሚያሳይ ስልጠናን በአሰልጣኝ አብርሀም አማካኝነት ማምሻውን ተሰጥቷል፡፡

ከባለፈው ሳምንት የቀጠለ የቡድን ግንባታ እና ሒደቱ በሚል ሰፊ ሽፋን ያለው ትምህርት በካፍ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ አማካኝነት ከሁለት ሰዓታት በላይ በፈጀ ቆይታ ተሰጥቷል፡፡ኢንስትራክተር አብርሃም በዋናነት በሞሮኮ በነበረ አንድ መድረክ ያቀረቡትን የቡድን ግንባታን በተመለከተ የተሰናዳውን ዝርዝር ትምህርቶችን ለሀገራችን አሰልጣኞች ሰጥተዋል፡፡

አንድ አሰልጣኝ ቡድን በምን መልኩ መገንባት አለበት፣ በልምምድ እና ከልምምድ ውጪ፣ በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት፣ በስነ ልቦና መሠረታዊ ግንባታ፣ በጨዋታ ውስጥ ተጫዋቾች ሊተገብሩት ስለሚገባ የሜዳ ላይ የቡድን ሥራ እና ተያያዥነት ያላቸውን ሀሳቦች ያዘለ የግንባታ መሠረታዊ ሀሳቦች በስልጠናው የተሰጡ ዋና ጉዳዮች ሲሆን የቡድን ውህደት እና ስብጥር እንዴት መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፤ ለማድረግስ ምን ምን ያስፈልጋል የሚሉም ኢንስትራክተሩ አንስተው ገለፃ አድርገውበታል፡፡ ስለ ቡድን ማንነት፣ የቡድን ግብ እና ውጤት ላይ ያተኮረ የውይይት ሀሳብ በአሰልጣኙ ተነስቶም ነበር፡፡

በመጨረሻም በአሜሪካ የሳክሪሜንቶ አካዳሚ አሰልጣኝ አምሳሉ ፋንታሁን የውይይት ሀሳብ አንስተው አሰልጣኞቹን ካወያዩ በኃላ የቪዲዮ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: