ከፍተኛ ሊግ | ሀላባ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ

አሰልጣኝ ደረጀ በላይ የሀላባ ከተማ አዲሱ አሰልጣኝ በመሆን በዛሬው ዕለት መሾማቸውን የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር ስርጋፋ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ የሚገኘው ሀላባ ከተማ በውል መጠናቀቅ ምክንያት ከአሰልጣኝ ካሊድ መሀመድ ጋር መለያየቱ ይታወሳል፡፡ ክለቡም በ2013 የውድድር ዓመት ጠንክሮ በመቅረብ ፕሪምየር ሊጉን ለመቀላቀል ልምድ ያለውን አሰልጣኝ ሲያፈላልግ ቆይቶ አሰልጣኝ ደረጃ በላይን በአንድ ዓመት ማስፈረሙን የሀላባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የክለቡ ፕሬዝዳንት አቶ አንዋር ስርጋፋ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡

ክለቦችን ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማሳደግ የተካኑት አሰልጣኝ ደረጀ በላይ ሰበታ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ዐምና ደግሞ ወልቂጤ ከተማን ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደግ የቻሉ ሲሆን በፕሪምየር ሊግ ደረጃም ጅማ እና ሰበታ ከተማን አሰልጥነው አልፈዋል፡፡ ወልቂጤ ከተማን በክረምቱ ለቀው ወደ ጌዲኦ ዲላ ተጉዘው ዘንድሮ ውድድሩ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ በክለቡ ቆይታን ካደረጉ በኃላ ሀላባን ለማሰልጠን ተስማምተዋል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!

error: