የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሲሆን አንድ አዲስ ቡድንም ለመጀመሪያ ጊዜ ይሳተፋል።
የሴካፋ የውድድር ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዩሱፍ ሞሲ የሴቶች የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ነሐሴ 26 በናይሮቢ ኬንያ እንደሚካሄድ ይፋ አድርገዋል። በዘንድሮው ማጣሪያ የሀገራችንን ተወካይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨምሮ 9 ክለቦች የሚሳተፉ ሲሆን የኤርትራው ደንደን ኤስሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ መሆኑም ታውቋል።
የዞኑ ማጣሪያዎች ከነሐሴ 29/2017 እስከ መስከረም 6/2018 በናይሮቢ በሚገኘው ናያዮ ስታዲየም እና ኡሊንዚ ኮምፕሌክስ ይካሄዳል።