የግብ ዘቡ የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

የግብ ዘቡ የቀድሞ ክለቡን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል

የ2016 የውድድር ዘመን የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ የሆነው ፍሬው ጌታሁን ወደ ቀድሞ ክለቡ ለማምራት ተቃርቧል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት ቆይታ የነበረው እና በ2016 ቡድኑ የሊጉን ዋንጫ ባነሳበት ዘመን ኮከብ ግብ ጠባቂነትን ክብር ያገኘው ፍሬው ጌታሁን ወደ ድሬደዋ ለማምራት መቃረቡን አውቀናል።

የእግርኳስ ጅማሮውን በሻሸመኔ ከተማ ያደረገው እና በከፍተኛ ሊግ በነገሌ አርሲ ተጫውቶ በመቀጠል ፈረሰኞቹን በመቀላቀለቅ በሁለት ዓመታት ቆይታ ሁለት የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ከቋጨ በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ፣ በድሬደዋ ከተማ ቆይታ ማድረጉ ይታወቃል። ያለፉትን ሁለት ዓመት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያሳለፈው የግብ ዘቡ በ2016 ሊጉን ዋንጫ ከማንሳቱ ባሻገር የወቅቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ መሆኑ ይታወሳል። አሁን ዳግም ወደ ቀድሞ ክለቡ ለማምራት መስማማቱን አውቀናል።