አህመድ ሁሴን ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

አህመድ ሁሴን ወደ ሌላ ክለብ አምርቷል

ከአዞዎቹ ጋር ለመቆየት ተስማመወቶ የነበረው ቁመታሙ አጥቂ ማረፊያው ሌላ ክለብ ሆኗል።

የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ተስማምቶ የነበረው ቁመታሙ አጥቂ አህመድ ሁሴን አሁን ማረፊያው አዳማ ከተማ መሆኑ ታውቋል።

የቀድሞው የወልቂጤ ከተማ ከዛም ደግሞ ረዘም ላሉ ዓመታት በአዞዎቹ ቤት ነግሦ የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነውን አህመድ ሁሴን ለሁለት ዓመት መዳረሻው አዳማ ከተማ መሆኑ ታውቋል።

አዳማ ከተማ አስቀድሞ ለማስፈረም ከተስማማቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ በቀጣዮቹ ቀናት ጠንከር ያሉ ዝውውሮች ለመፈፀም ስራዎች እየሰራ መሆኑን ከክለቡ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።