የመስመር ተከላካዩ ከሲዳማ ቡና ጋር ለመቀጠል ተሰምቷል

የመስመር ተከላካዩ ከሲዳማ ቡና ጋር ለመቀጠል ተሰምቷል

ሲዳማ ቡናዎች የነባር ተጫዋቾችን ውል ለማራዘም መስማማታቸውን ቀጥለዋል።

ቅድመ ዝግጅታቸውን ከቀናት በኋላ የሚጀምሩት ሲዳማ ቡናዎች አስቀድመው ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች በተጨማሪ በትናትናው ዕለት የክለቡ የበላይ አካሎች ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ለማቆየት ማናገራቸውን እና ከሰዓታት በፊት አማካይ ዮሴፍ ዮሐንስን ለማቆየት መስማማታቸውን ዘግበን ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ደግሞ የብርሃኑ በቀለ ለመቆየት መስማማታቸውን አውቀናል።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 26 ጨዋታዎች ተሳትፎ 2156′ ደቂቃዎች ቡድኑን ያገለገለው ተጫዋቹ ከኋላ እየተነሳ ሁለት ግቦች ማስቆጠሩም ይታወሳል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በደቡብ ፓሊስ በነበረው ቆይታ ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊግ በማሳደግ ራሱን በሊጉ ያስተዋወቀ ሲሆን በመቀጠል ሀዋሳ ከተማ፣ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ ማድረጉም ይታወሳል።