በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።
በዝውውር መስኮቱ ፍሬው ሰለሞን፣ በየነ ባንጃው፣ ኢብራሂም መሐመድ፣ ሰመረ ሀፍታይ፣ ጌትነት ተስፋዬ፣ ፍቃዱ መኮንን፣ ነፃነት ገብረመድህን፣ ሙሉዓለም መስፍን፣ ኮንኮኒ ሀፊዝ እና ወጋየሁ ቡርቃን አስፈርመው የሰባት ነባር ተጫዋቾችን ውል ያራዘሙት ወልዋሎዎች ዛሬ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።
ባለፈው የውድድር ዓመት በአስራ ዘጠኝ ነጥቦች በሊጉ ግርጌ ላይ ሆነው ዓመቱን ያጠናቀቁት ቢጫዎቹ በ2018 የውድድር ዓመት ተጠናክረው ለመቅረብ በዝውውር መስኮቱ ካደረጉት ንቁ እንቅስቃሴ በኋላ ዛሬ በአዳማ ከተማ በ’ጂምናዝየም’ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ደግሞ ወደ ሜደ እንቅስቃሴ እንደሚገቡ እና በቀጣይ በሀገሪቱ ይካሄዳሉ ተብለው ከሚጠበቁ የቅድመ ዝግጅት ውድድሮች በአንዱ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።