ያለፈውን አንድ ዓመት በቡርትካናማዎቹ ቤት ቆይታ አድርጎ የነበረው የግብ ዘብ ወደ ሌላ የሊጉ ክለብ ለማምራት ተስማምቷል።
ቅድመ ዝግጅታቸውን በሀዋሳ ከተማ ላይ የጀመሩት ሲዳማ ቡናዎች የግብ ጠባቂውን መስፍን ሙዜ ፣ ደግፌ ዓለሙ ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ ፣ ብርሃኑ በቀለ እና ይገዙ ቦጋለን ውል ለማራዝም ተስማምተው ያሬድ ማቲዮስ ፣ ሞገስ ቱሜቻ እና ተመስገን በጅሮንድ ወደ ክለባቸው ማምጣታቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የግብ ዘቡን አላዛር ማረነ ለማስፈረም ተስማምተዋል።
ከዚህ ቀደም በገላን ከተማ ያሳለፈው የግብ ዘብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከከፍተኛ ሊግ ሲያድግም የሊጉን ዋንጫ ሲያነሳ የቡድኑ አካል የነበረ ሲሆን ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ቡርትካናማዎቹ ቤት ቆይታ ካደረገ በኋላ አሁን ሲዳማ ቡናን ለሁለት ዓመት ለማገልገል መስማማቱን አውቀናል።
