👉”ካፍ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ካታጎሪ ሁለት ጨዋታን ለማድረግ አይመጥንም …
👉”የመልሱን ጨዋታ አዲስ አበባ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው…
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በ2026 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከታንዛንያ ጋር ለሚያደርጋቸው ወሳኝ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ያደረገውን ዝግጅት በተመለከተ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የመሰብሰብያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። በመግለጫውም ላይ የፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ወቅታዊ ሁኔታ ዙርያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
“እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም የአበበ ቢቂላ ስታዲየም አንደኛ እና ሁለተኛ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በክለቦች እና በሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ይካሄድበት ነበር። ሆኖም የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታውን በሚያደርግበት ወቅት ሜዳው ውሃ መያዙን ተከትሎ እና ወላይታ ድቻ እና ኢትዮጵያ መድን ባደረጉት የካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ኮፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታ ላይ የጨዋታው ኮሚሽነሮች ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት ካፍ የአበበ ቢቂላ ስታዲየም የአበበ ቢቂላ ስታዲየም ካታጎሪ ሁለት ጨዋታን ለማድረግ አይመጥንም የካፍን ሚኒመም መስፈርት ማሟላት አይችልም ብሎ አሳውቆናል።”
“እንዲሁም ሌላ ገለልተኛ ሜዳ አሳውቁ ብንባልም ፌዴሬሽኑ ከክለብ ላይሰንሲግ ኃላፊ ጋር በመሆን ውሳኔውን ባለ መቀበለ አበበ ቢቂላ ማጫወት ይችላል እንዲሁም የድሬደዋ ስታዲየምም አለን በተጨማሪም የአዲስ አበባ ስታዲየምንም በአማራጭ አቅርበናል። ዛሬ የካፍ ገምጋሚ ቡድን አዲስ አበባ ይገባል። ሦስቱን ሜዳዎች ገምግመው የመልሱ ጨዋታ በሀገራችን እንዲደረግ ስራ እየሰራን ነው” ብለዋል።