የተራዘመው የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀን ተቆጠረለት

የተራዘመው የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀን ተቆጠረለት

ተራዝሞ የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ 4ኛ ዙር ውድድር መች እንደሚደረግ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

የ2018 የኢትዮጵያ ዋንጫ የ4ኛ ዙር የውድድር ፕሮግራም በቀን 25/05/2018 ለቡድኖች ቀድሞ ተልኮ ከመጋቢት 12-15 ሊከናወኑ የነበሩ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገራቸው ይታወሳል።

ዛሬ ፌዴሬሽኑ ለቡድኖች በላከው ደብዳቤ ላይ እንደገለጸው ከሆነ ደግሞ ከዚህ በታች ምስሉ ላይ የተያያዘው መርሐግብር ይፋ መደረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።