በአሰልጣኝ መሠረት ማኔ የሚመራው መቻል ሁለት ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአራት ተጫዋቾቹን ውል ደግሞ አራዝሟል።

በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 56 ነጥቦችን በመሰብሰብ ሦስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው መቻል ለቀጣይ የውድድር ዘመን ቡድኑን ማዘጋጀት ጀምሯል። የቀድሞ ተጫዋቹን የመስመር ተከላካይዋን ፀሐይነሽ ጁላን ከሐዋሳ እንዲሁም የተከላካይ አማካይዋን ዙፋን ደፈርሻን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ያስፈረመው ቡድኑ የጽዮን ፈየራ ፣ ቱፊት ካዲዮ ፣ ትዕግሥት ወርቄ እና ነጻነት ጸጋየን ውል ደግሞ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት ማራዘሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

