በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመሩት ሀዋሳ ከተማዎች የሁለት ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል።

ቀደም ሲል የዳዊት ታደስን እና የቸርነት አውሽን ውል ያራዘሙት ሀዋሳ ከተማዎች አሁን ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን ለተጫማሪ ሁለት ዓመታት በክለባቸው ለማቆየት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የመጀመሪያው ውሉን ያደሰው ግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራ ነው። ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ከተገኘ በኋላ ለሀዋሳ ከተማ ወጣት ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወጣት ብሔራዊ ቡድን የተጫወተ ሲሆን በቀድሞው አጠራሩ ለዲላ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ እንዲሁም ወደ ሀዋሳ ከተማ በመመለስ ዋናው ቡድን አገልግሎ ሁለት የውድድር ዘመናት በመቻል ቆይታ ካደረገ በኋላ በአዳማ ከተማ ቀጥሎም በአሁኑ ክለቡ ሀዋሳ ከተማ የተጠናቀቀውን ውድድር ዓመት በመጫወት ያሳለፈ ሲሆን ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ለመቆየት ተስማምቷል።
ሁለተኛው ውሉን ያደሰው ፊቃደሥላሴ ደሳለኝ ነው። ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ ላለፉት ዓመታት ክለቡን ሲያገለግል የነበረው የመስመር ተከላካዩ ከአሳዳጊው ጋር ለመቆየት ስምምነት ላይ ደርሷል።

