አቤኔዘር ዓለማየሁ ዛሬ ወደ ዩክሬን ይጓዛል

አቤኔዘር ዓለማየሁ ዛሬ ወደ ዩክሬን ይጓዛል


የጦና ንቦቹ ተስፈኛ ወጣት ወደ አውሮፓዊቷ ሀገር ዩክሬን ሊያቀና ነው

መነሻው በጦና ንቦቹ ከ17 ዓመት በታች ቡድን አድርጎ ዘንድሮ ለመጀመርያ ጊዜ ወደ ዋናው ቡድን ማደግ የቻለው የግራ መስመር አጥቂው አቤኔዘር ዓለማየሁ ዛሬ ዕኩለ ለሊት ወደ ዩክሬን እንደሚያቀና ለተጫዋቹ ዕድሉን ያመቻቸው ፊፋ ኤጀንት ዳዊት አርጋው መረጃውን አድርሶናል።

አቤኔዜር የሚያቀናበት ክለብ የዩክሬኑ ፖሊስያ ዝሂቶሚር እግር ኳስ ክለብ ነው ፤ ቡድኑ በዩክሬን በዚቶሚር ፖሊስያ የሚገኝ ክለብ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ፕሪምየር ሊግ በመሳተፍ ላይ የሚገኝ እና በደረጃ ሰንጠረዡ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ክለብ ነው። አቤኔዜር የሚያደረገው የሙከራ ዕድል ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር ሲሆን በሚሰጠው የሙከራ ወቅት ውጤታማ ከሆነ ዕድሜው 18 ዓመት ሲሞላው ለዋናው ፖሊስያ ዝሂቶሚር ቡድን የሚፈርም ይሆናል።

አቤኔዘር ይህን ድል ሊያገኝ የቻለው ሀገራችን ከ22 ዓመታት በኋላ ሀገራችን ወደ አፍሪካ መድረክ እንድትመለስ ባደረገው የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ባሳየው ድንቅ ብቃት እና በሞሮኮ አስተናጋጅነት በተዘጋጀው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ባሳየው ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እንደሆነም ሰምተናል።