ይገዙ ቦጋለ ወደ አሳዳጊው ክለብ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል

ይገዙ ቦጋለ ወደ አሳዳጊው ክለብ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል

በተጠናቀቀው ዓመት ከአዞዎቹ ጋር ያሳለፈው አጥቂ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ እናት ክለቡ ለመመለስ ከጫፍ ደርሷል።

በተጠናቀቀው ዓመት በአርባምንጭ ከተማ ቆይታ ያደረገው አጥቂው ይገዙ ቦጋለ ከአንድ ዓመት የአዞዎቹ ቆይታ በኋላ ወደ እናት ክለቡ ሲዳማ ቡና ለመመለስ ከጫፍ ደረሰ።  በ2014 ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የነበረው አጥቂው ከሲዳማ ቡና ታዳጊ ቡድን ካደገ በኋላ በዋናው ቡድን ለስድስት ዓመታት ያገለገለ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአንድ ዓመት የአርባምንጭ ከተማ ቆይታ በኋላ ዳግም ወደ ሲዳማ ቡና ለመመለስ የመጨረሻው ድርድር በማድረግ ላይ ይገኛል።

የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም ወደ ክረምቱ  የዝውውር መስኮት ከገቡ በኋላ አዳዲስ ተጫዋቾች ወደ ስብስቡ በመቀላቀል ለአፍሪካ ቻምፕዮንስ ሊግ በመዘጋጀት ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ከቀናት በፊት ዝግጅት መጀመራቸው ይታወሳል።