ከሸገር ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው አማካዩ መዳረሻው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል።

ለ2019 የውድድር ዓመት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾችን ውል በማራዘም ቡድናቸው ለማጠናከር እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች አሁን የናትናኤል ዘለቀን ዝውውር አጠናቀዋል።
ናትናኤል በቅዱስ ጊዮርጊስ ከዋንጫ ጋር የታጀበ ስኬታማ የዓመታት ቆይታ ወደ ወልዋሎ አቅንቶ የነበር ሲሆን ዘንድሮ በተጠናቀቀው ውድድር ዓመት ለሸገር ከተማ የተጫወተ ተጫውቷል። አሁን ደግሞ ለሁለት ዓመታት ከቀድሞ አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ ጋር ሊሠራ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ፈርሟል።

