የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።

የነባር ተጫዋቾች ውል በማራዘም እንዲሁም አዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም ለሚጠብቃቸው የካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ስብስባቸውን በማጠናከር ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ አማር ፋል ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
በሴኔጋል ሊግ አንድ ተሳታፊ በሆኑት የሀገሩ ክለቦች ሳናኮስ እና ፒኪን በመጫወት ላይ የቆየው ይህ የ 23 ዓመቱ ተጫዋች በሴኔጋል ሊግ አንድ ጠንካራ የተከላካይ ክፍል ከነበረባቸው ክለቦች አንዱ በነበረው ፒኪን በሀያ አራት ጨዋታዎች ተሳትፎ በአስራ አራቱ ግቡን ሳያስደፍር የወጣ ሲሆን አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልዋሎ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውን ዩጋንዳዊ ሙታክብዋ ጆኤልን ለመተካት ወደ ክለቡ ለማምራት ከስምምነት ደርሷል።

