ሐይቆቹ ከወጣት ቡድን አራት ታዳጊዎችን ወደ ዋናው ቡድን አሳድገዋል።

በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሚመራው ሀዋሳ ከተማ ለወጣቶች ትኩረት የመስጠት ባህሉን በማስቀጠል ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ አራት ተስፈኛ ተጫዋቾችን ወደ ዋናው ስብስብ አሳድጓል።
ወደ ዋናው ቡድን ያደጉት አቤኔዘር ወንድሙ እና ዘሪሁን ኃይለማርያም በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወቱ ሲሆን፣ ሀብታሙ ገና እና ካሌብ ዶጊሶ ደግሞ የፊት መስመር አጥቂዎች ናቸው። ታዳጊዎቹ ቡድኑ ዛሬ ከኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር ባደረገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ላይ ሲጫወቱ ተመልክተናል።

