ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለፉትን አራት ዓመታት ቆይታ የነበራት አሰልጣኝ ቀጣይ ማረፊያዋ መቻል መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።
በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ከሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው መቻል በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተቋሙ ሲሾም የነበረውን የአሰልጣኝነት መንበር ቦታን ለመጀመሪያ ጊዜ ፊቱን ወደ ውጪው በማዞር ሁለት አሰልጣኞችን ሲያፎካክር ቆይቶ በመጨረሻም አሰልጣኝ መሠረት ማኔን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
የድሬዳዋ ከተማን የሴቶች ቡድንን በኋላም ደግሞ በ2008 የወንድ ቡድኑን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ማሳደግ የቻለችው አሰልጣኝ እና የካፍ ኢንስትራክተሯ መሠረት ማኔ በመቀጠል በአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ላለፉት አራት ዓመታቶች ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመምራት በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ በማድረግ በቡድኑ ውስጥ ቆይታን አድርጋለች። አሁን ደግሞ ወደ መቻል በማምራት የቡድኑ አሠልጣኝ መሆኗ ታውቋል።
