ያለፉትን ሁለት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታ የነበረው የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ውሉን ማራዘሙ ታውቋል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚሰለጥኑት ሲዳማ ቡናዎች ከዚህ ቀደም የግብ ዘቡን መስፍን ሙዜ እና የተከላካዩ ደግፌ አለሙን ውል ሲያራዝሙ ከከፍተኛ ሊግ ደግሞ የተከላካዩቹን ያሬድ ማቲዮስ እና ሞገስ ቱሜቻን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የተከላካይ አማካዩ ዮሴፍ ዮሐንስን ውል ማራዘማቸው ይታወቃል።
በሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን የተገኘው ዮሴፍ በሲዳማ ቡና ለአምስት ዓመታት ካገለገለ በኋላ በመቀጠል በአደማ ከተማ እና በድሬደዋ ከተማ ቆይታ በማድረግ ዳግም ወደ ቀደሞ ክለቡ በመመለስ ያለፉትን ሁለት ዓመት ቡድኑን ማገልገሉ ይታወቃል። ትናት ከክለቡ ቦርድ ጋር ባደረገው ድርድር ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት መስማማታቸውን አውቀናል።
ሲዳማ ቡና በቀሩት የዝውውር ቀናቶች ተጨማሪ ውል የማራዘም እና አዳዲስ ተጫዋቾችን የማስፈረም ስራዎችን እንደሚሰሩ አውቀናል።