በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተጫዋች ከአራት ዓመታት በኋለ ወደ ሲዳማ ቡና ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚሰለጥኑት ሲዳማ ቡናዎች ከዚህ ቀደም የመስፍን ሙዜ፣ ደግፌ ዓለሙ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ እና ብርሀኑ በቀለን ውል ለማራዝም ተስማምተው የተከላካዩቹን ያሬድ ማቲዮስ እና ሞገስ ቱሜቻን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በመቐለ 70 እንደርታ ቆይታ የነበረው ተመስገን በጅሮንድን ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በአማካይ እንዲሁም በአጥቂ ቦታ ላይ መጫወት የሚችለው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም በሺንሺቾ ከተማ ፣ ደደቢት ፣ ኢኮስኮ፣ ሲዳማ ቡና፣ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም መቐለ 70 እንደርታ መጫወቱ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአራት ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ ሲዳማ ቡና ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።