የ2014 ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የነበረው አጥቂ በክለቡ ለተጨማሪ ዓመት ለመቆየት ተስማምቷል።
አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም የነባር ተጫዋቾችን ውል እያራዘመ የሚገኘው ሲዳማ ቡና አሁን ደግሞ ያለፉትን ስድስት ዓመት በዋናው ቡድን እየተጫወተ ያሳለፈውን ይገዙ ቦጋለን ለተጨማሪ ዓመት ለማቆየት ተስማምተዋል።
ከሲዳማ ቡና መለያ ውጭ ሌላ ማልያ ለብሶ የማያውቀው ይገዙ ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋና ቡድን በሲዳማ ቡና አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን አሁን ደግም በአሳዳጊ ክለቡ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት መስማማቱ ታውቋል። አጥቂው በ2015 የውድድር ዘመን የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ማጠናቀቁ ይታወሳል።