በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማን ይሆናል?

በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማን ይሆናል?

👉”በተጫዋችነት ዘመኑ ትልቅ ክብር የምንሰጠው ነው። ወደ አሰልጣኝነትም ከመጣ በኋላ….

👉”ከውጤት አንፃር እግርኳሳችን ያለበት ሁኔታ የሚያስደስት አይደለም።”

በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማን ይሆናል? አሰልጣኝ ካሳዬ መሆን ይችል ይሆን በሚል ለተነሳው ጥያቄ አቶ ባህሩ ጥላሁን ምላሽ ሰጥተዋል።

በሦስት አመት ከስድስት ወር ውስጥ አራት አሰልጣኞች ተቀያይረዋል ውጤትም እየመጣ አይደለም። ይህን ተከትሎ በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝ መሳይ ይቆያል ወይስ የውጭ ሀገር አሰልጣኝ ይቀጥራ? እንዲሁም አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ብሔራዊ ቡድኑ ለምን አያሰለጥንም በሚል ከመገናኛ ብዙሀን ለተነሳባቸው ጥያቄ አቶ ባህሩ ተከታዮን ምላሽ ሰጥተዋል።

“በተጠቀሱት ዓመታቶች ውስጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተለያዩ አሰልጣኞች በጊዜያዊነት እና በዋናነት መርተዋል ከዚህ ሂደት ውስጥ ፌዴሬሽኑ ያሰናበተው አሰልጣኝ የለም። ከአሰልጣኝ ውበቱ ጋር በስምምነት ከተለያየን በኋላ ሌሎቹ አራት አሰልጣኞች ኮንትራት ማብቃት ጋር ተያይዞ የለቀቁ ናቸው። ከውጤት አንፃር እግርኳሳችን ያለበት ሁኔታ የሚያስደስት አይደለም። በቀጣይ ስለሚሆነው አሰልጣኝ ስራ አስፈፃሚ የሚያደርገው ስብሰባ ይኖራል። አዳዲስ ነገሮችን የሚኖሩ ከሆነ የምናሳውቅ ይሆናል።”

“በተጫዋችነት ዘመኑ እጅግ የምናከብረው ክብር የምንሰጠው ነው። ወደ አሰልጣኝነትም ከመጣ በኋላ የራሱን ሀሳብ ለመተግበር እየሞከረ ያለ አሰልጣኝ ነው። ካሳዬን በተመለከት ጥያቄው ተነስቷል። ከአጨዋወቱ ሀሳብ በዚህ ዙርያ እኔ ቴክኒካል የሆነ ነገር ስለሆነ ሀሳብ አልሰጥም ብለዋል።”