ሲዳማ ቡና ቅድመ ዝግጅቱን ጀምሯል

ሲዳማ ቡና ቅድመ ዝግጅቱን ጀምሯል

ሲዳማ ቡናዎች ለመጪው የውድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅታቸውን ዛሬ መጀመራቸውን አረጋግጠናል።

በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚሰለጥኑት ሲዳማ ቡናዎች የመስፍን ሙዜ ፣ ደግፌ ዓለሙ ፣ ዮሴፍ ዮሐንስ ፣ ብርሃኑ በቀለ እና ይገዙ ቦጋለን ውል ለማራዝም ተስማምተው የተከላካዩቹን ያሬድ ማቲዮስ ፣ ሞገስ ቱሜቻ እና ተመስገን በጅሮንድን ዝውውር ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

የነባሮቹን ውል እያራዘሙ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እየቀላቀሉ የሚገኙት ሲዳማ ቡናማዎች በትናንትናው እለት በሀዋሳ ታደሰ እንጆሪ ሆቴል ከተሰበሰቡ በኋላ ዛሬ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ሰርተዋል።