በሊብያው ክለብ ቆይታ የነበረው ኢትዮጵያዊው አማካይ ወደ ኦማኑ ክለብ አምርቷል።
በተጠናቀው ዓመት በሊብያ ክለቦች አል መዲና እና ሸባብ አል ግሀር ቆይታ የነበረው ከነአን ማርክነህ ከሊብያው ክለብ የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ኦማኑ አል ሸባብ አምርቷል። ተጫዋቹ ቀደም ብለን እንዳጋራናቹህ ከሊብያው ክለብ የውል ማራዘምያ ጥያቄ ቢቀርብበትን ወደ ኦማኑ ክለብ ለማምራት ተስማምቶ የሕክምና ምርመራውን አጠናቋል።
በሁለቱ የሊብያ ክለቦች ቆይታው በአስራ አራት ጨዋታዎች ተሳትፎ ስድስት ግቦች ያስቆጠረው ተጫዋቹ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአሜሪካ ቆይታው ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመልማዮች ዓይን ውስጥ ገብቶ ከክለቡ ጋር ቆይታ ማድረግ ቢችልም አሁን በሰሜን ኦማን ባርካ ከተማ ተቀማጭነቱ ያደረገው በአሰልጣኝ ሀሰን ሩስታም ወደሚመራው አልሸባብ አቅንቷል።