የሉሲዎቹ የወቅቱ አንበል የግብ ዘቧ ታሪኳ በርገና ከወሳኙ ጨዋታ አስቀድሞ ምን አለች።
የፌዴሬሽኑ የፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን እና የሉሲዎቹ ዋና አለቃ አሰልጣኝ ዮሴፍ ከታንዛርያ ጋር ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚያደርጉትን ፍልሚያ አስመልክቶ ከሜዳ እና ከሜዳ ውጭ ያሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ የሰጡትን ማብራሪያ አስነብበናቹሁ ነበር። አሁን ደግሞ የሉሲዎቹ የወቅቱ አንበል የግብ ዘቧ ታሪኳ በርገና ከወሳኙ ጨዋታ አስቀድሞ ስለ ጨዋታው ያላትን ሀሳብ አጋርታለች
“ ኢትዮጵያ በሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ ካለፈች አስራ አራት አመት ሆኗል። ይህ ስብስብ ታሪክ ለመስራት ተዘጋጅቷል። ቡድናችን አቅም ያለውና ታሪክ ለመስራት ዝግጁ ነው። የቡድናችን ህብረት፣ አንድነት መንፈሳችም ጥሩ ነው። ፌዴሬሽኑም በሁሉም መልኩ እያገዘን ነው በዚህም ማመስገን እፈልጋለው።” ካለች በኋላ “በሜዳችን በምናደርገው የመልስ ጨዋታም ህዝቡ ሁሌም እየደገፈ ነው አሁን እኛ ታሪክ ለመስራት በእኛ በኩል ዝግጁ ነን የኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ እንዳይለየን ጥሪዬን አቀርባለው።” ብላለች።
