ካፍ በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ዙርያ አዲስ ውሳኔ አስተላለፈ

ካፍ በሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ዙርያ አዲስ ውሳኔ አስተላለፈ

ካፍ በቶታል ኢነርጂስ ካፍ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሀገራት ቁጥር እንዲጨር ውሳኔ አስተላልፏል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በቶታል ኢነርጂስ ካፍ የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ የሚሳተፉ ሀገራት ቁጥር ከአስራ ሁለት ወደ አስራ ስድስት ቡድኖች ከፍ እንዲል ውሳኔ አሰተላለፈ። የአፍሪካ እግር ኳስ በበላይነት የሚያስተዳድረው ይህ ተቋም የማጣርያ ሂደቱ ቢጠናቀቅም አራት ቡድኖች ወደ ውድድሩ እንዲቀላቀሉ በወሰነው መሰረት በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር ከተሰናበቱ ሀገራት ውስጥ በወቅታዊው የፊፋ ሀገራት ሰንጠረዥ የተሻለ ደረጃ የያዙት ካሜሮን፣ ኮትዴቭዋር ፣ ማሊ እና ግብፅ በውድድሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ውሳኔ አስተላልፏል።

ካፍ የተሳታፊ ሀገራት ቁጥር ይጨምራል የሚሉ ዜናዎች መሰራጨት ከጀመሩ በኋላ ወደ ውድድሩ የሚያቀኑ ሀገራት በደርሶ መልስ ጨዋታዎች ይለያሉ የሚሉ መላ ምቶች እየተሰሙ ቢቆዩም ተቋሙ ይህንን ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ በመጨረሻው የማጣርያ ጨዋታ በታንዛንያ አቻቸው ሽንፈት ያስተናገዱት ሉሲዎቹ በውድድሩ የመሳተፍ ዕድላቸው አክትሞለታል።