ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ የሚጠብቃት ማላዊ የ23 ተጫዋቾች ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።
ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 በድሬዳዋ ስታዲየም በኢትዮጵያ እና ማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን ለዚህ ጨዋታ ማላዊዎች እንደ ዋልያዎቹ ሁሉ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

የነበልባሎቹ ዋና አሰልጣኝ ካሊስቶ ፓሱዋ ጥሪ ካደረጉላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል 14ቱ ከሀገር ውጪ የሚጫወቱ ተጫዋቾች መሆናቸው ሲታወቅ ሉቺያኖ ማቲው ፣ ክርስቶፈር ኩምዌምቤ እና ፍራንሲስኮ ማዲንጋ ለብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሪ የደረሳቸው ተጫዋቾች ናቸው።
አሰልጣኙ “የነባር ተጫዋቾችን ጠንካራ እና ደካማ ጎን እናውቃለን። አሁን ሌሎች ተጫዋቾችን በመሞከር ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያው የተሻለ ስብስብ እንዲኖረን እናደርጋለን።” ብለዋል።
በብላንታየር ከተሰበሰቡ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በረራ እንደሚያደርጉ የሚጠበቁት 3 ግብ ጠባቂዎች ፣ 5 ተከላካዮች ፣ 7 አማካዮች እና 8 አጥቂዎች ዝርዝር በምስሉ ላይ ተያይዟል 👇


