ወልዋሎ የሚያደርጋቸው የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኙ ታውቋል።

ወልዋሎ ከሊብያው ክለብ አል አህሊ ትሪፖሊ የሚያደርጋቸው ሁለት የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን ያገኛሉ። በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የሚካሄዱትን
ጨዋታዎች በቀጥታ ለማስተላለፍ ፈቃድ ያገኘው ተቋም ደግሞ ‘Hassad TV’ መሆኑ ታውቋል።
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ ውድድር በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ወልዋሎ በመጀመሪያው ዙር የሱዳኑን ሂላል አል ሳሕልን አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፉ የሚታወስ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎቹም ጥቅምት 6 እና ጥቅምት 13 በሊብያ መዲና በትሪፖሊ ኢንተርናሽናል ስታድየም ያደርጋል።

