ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ የቀረው የጋና እና ኢትዮጵያ ጨዋታ ዛሬ 09:00 ላይ ይካሄዳል፡፡
ጨዋታው ትላንት 12:00 ሊካሄድ ፕሮግራም ወጥቶለት የነበረ ቢሆንም በኬፕኮስት በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ሳይካሄድ መቅረቱ የሚታወስ ነው፡፡
አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የመጀመርያ ጨዋታ ኢትዮጵያ 2-1 ማሸነፏ የሚታወስ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ሜዳ ይዛው የምትገባው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል፡-
1 ተክለማርያም ሻንቆ
8 እንየው ካሳሁን – 2 ሃይደር ሙስጠፋ – 6 ተስፋዬ ሽብሩ – 7 ደስታ ደሙ
16 ዘላለም ኢሳያስ – 13 ዘሪሁን ብርሃኑ (አምበል)
17 ዳዊት ማሞ – 11 ዳዊት ተፈራ – 15 ሚካኤል ለማ
9 አሜ መሃመድ