የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ 2ኛ ዙር ዛሬ በተደረጉ የ11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ሲጀመሩ ሀዋሳ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና አዳማ አሸንፈዋል፡፡ ወደ ባህርዳር የተጓዘው ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ከጥረት ነጥብ ተጋርቷል፡፡
ምድብ ሀ
አዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን አስተናግዶ 1-0 አሸንፏል፡፡ አዳማ ድሁን ተከትሎ ነገ ጨዋታውን ከሚያደርገው ደደቢት ጋር ነጥቡን አስተካክሏል፡፡ ባህርዳር ላይ ጥረት ኮርፖሬት ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ 1-1 በሆነ አቻ ውጤት የተለያዩበት የዚህ ምድብ ሌላው ጨዋታ ነበር፡፡
[table id=196 /]
[league_table 18073]
ምድብ ለ
ሀዋሳ ላይ ልደታ ክፍለከተማን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 4-0 በማሸነፍ ወደ ድል ተመልሷል፡፡
በ28ኛው ደቂቃ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቿ ትርሲት መገርሳ አመቻችታ ያቀበለቻትን ኳስ አጥቂዋ አይናለም አሳምነው ግብ አስቆጥራ ሀዋሳን ቀዳሚ አድርጋ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
በ58ኛው ደቂቃ እንደመጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ በጨዋታው ጥሩ የነበረችው ትርሲት መገርሳ አሾልካ ያቀበለቻትን ኳስ አይናለም አሳምነው ለሀዋሳ ሁለተኛ ግብ አስቆጥራለች፡፡ ትርሲት የቡድኑን 3ኛ ግብ ከርቀት በመምታት ስታስቆጥር አይናለም አሳምነው በ81ኛው ደቂቃ ሐት-ትሪክ የሰራችበትን ግብ በማስቆጠር ጨዋታው በሀዋሳ 4-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
በሀዋሳ ከተማ በኩል ቅድስት ዘለቀ በከባድ ጉዳት ከሜዳ 76ኛ ደቂቃ ወታለች በወጣችበት ሰአት አምቡላንስ ዘግይቶ መምጣቱ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ቅድስት ማርየያም ያደረጉት ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ጊዮርጊሶች በመሰሉ አበራ የቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ ሲሆኑ መዲና አወል ከእረፍት መልስ ቅድስት ማርያምን አቻ አድርጋለች፡፡ ፈረሰኞቹ አሸንፈው የወጡበትን ወሳኝ ግብ ያስቆጠረችው የመስመር ተከላካይዋ ሒሩት ደምሴ ናት፡፡
[table id=197 /]
[league_table 18083]