ሴቶች ዝውውር | አዳማ ከተማ አራት ተጫዋቾች አስፈርሟል

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮት ከተከፈተ አንድ ወር ቢያስቆጥርም ክለቦች እምብዛም በዝውውር ላይ እየተሳተፉ አይገኙም። ዓመቱን በ5ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው አዳማ ከተማ ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ሁኔታ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያለ ክለብ ሲሆን አራት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል። 

ሳራ ነብሶ አዳማ ከተማ ካስፈረማቸው ተጫዋቾች አንዷ ናት። የአጥቂ መስመር ተጫዋቿ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በጌዴኦ ዲላ 10 ጎሎችን አስቆጥራ ድንቅ ጊዜን ማሳለፍ የቻለች ተጫዋች ናት። በመከላከያ ያለፉት አራት የውድድር ዓመታት የተመለከትናት አክበረት ገብረፃዲቅ ሌላዋ የአዳማ ከተማ ፈራሚ ስትሆን የሲዳማ ቡና አምበል የነበረችው ነፃነት ብርሀኑ እና የድሬዳዋ ከተማዋ ተከላካይ ትዕግስት ንጉሴ አዳማ ከተማን ተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ በዝውውር መስኮቱ ተጨማሪ ተጫዋቾች ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የደደቢቶቹ አልፊያ ጃርሶ እና እፀገነት ብዙነህን ለማስፈረም እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተነግሯል።