ፋሲል ከነማ ጋናዊውን አማካይ አስፈርሟል

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ረዘም ያለ ቆይታ ያለው ጋናዊው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ጋብርኤል አህመድ ዐፄዎቹን ተቀላቅሏል፡፡

ጋናዊው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ጋብሬል አህመድ በ2003 ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በደደቢት የተሳካ ጊዜያት ካሳለፈ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ ተጫውቷል። ዐምና ደግሞ ወደ መቐለ 70 እንደርታ በማምራት ከቡድኑ ጋር የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን በማንሳት የደደቢት ድሉን በመቐለ መድገም ችሏል።

አሰልጣኝ ሥዩም ከበደን ከቀጠረ በኋላ በዝውውሩ መቀዛቀዞች ታይተውበት የነበረው ክለቡ ጋብሬልን በአንድ ዓመት ውል የመጀመርያ ፈራሚያቸው ሲያደርግ ከአሰልጣኙ በፊት እንየው ካሣሁን እና ኪሩቤል ዳኛቸው መፈረማቸው የሚታወስ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

error: