ባህር ዳር ከተማ የሴቶች ቡድን ሊመሰርት ነው

በ1973 የተመሰረተው ባህር ዳር ከተማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች ቡድን ለማቋቋም ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል።

ባሳለፍነው ዓመት አዳዲስ አመራሮችን ወደ ክለባቸው ያመጡት ባህር ዳር ከተማዎች አወቃቀራቸውን በአዲስ መልክ በማደራጀት ሥራዎችን ለመስራት መዘጋጃታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል። ለመስራት ካሰቧቸው ስራዎች መካከልም የሴቶች ቡድን ማቋቋም የሚለውን ለመተግበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማገባደዳቸው ተነግሯል።

የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ልዑል ፍቃዱ ለሶከር ኢትዮጵያ እንደገለፁት ከሆነ ቡድኑ በእርግጠኝነት ዘንድሮ እንደሚመሰረት እና ከሁለተኛ ዲቪዚዮን ጀምሮ ውድድር እንደሚያደርግ ተናግረዋል። አቶ ልዑል ጨምረውም በቀናት ውስጥ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ደብዳቤ እንደሚልኩ እና የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ እንደሚያወጡ አስረድተዋል።

ምንም እንኳን ሥራ አስኪያጁ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ እናወጣለን ብለው ሃሳብ ቢሰጡም የቀድሞ የጥረት ኮርፖሬት አሰልጣኝ ሰርካዲስ ጉታ ክለቡን እንደምትይዝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ