የአሰልጣኞች አስተያየት | ስሑል ሽረ 1-0 ኢትዮጵያ ቡና

ስሑል ሽረ በዲዲዬ ለብሪ ብቸኛ ግብ ኢትዮጵያ ቡናን ካሸነፈ በኃላ የሁለቱ ቡድን አሰልጣኞች የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል።
“በርካታ ዕድሎች ፈጥረን ወደ ጎል መቀየር አልቻልንም” ሳምሶን አየለ – ስሑል ሽረ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። የሊጉ የመጀመርያ ጨዋታ እንደመሆኑ ለቀጣይ ለውድድሩ የበለጠ በሞራል እንድንቀጥል የሚያደርግ እና የሚያነሳሳ ድል ነው። ሌላው በቅድመ ውድድር የነበሩንን ክፍተቶች ለማረም ያደረግናቸው እንቅስቃሴዎች አግዘውናል። ቡናዎች ኳስ ከኃላ ጀምረው ለመምጣት የሚያደርጉት ጥረት ስለነበረ ይሄን እንቅስቃሴያቸውንም በአዲስ አበባ ዋንጫ አይተነው ስለነበር ለዛ በቂ ዝግጅት ነበር ያደረግነው።

የሚፈለገውን ውጤት አምጥተናል። ብዙ ኳሶች ያንሸራሸሩት እኛ በፈቀድንላቸው የሜዳ ክፍል ነበር። በሁለቱም አጋማሾች ተጭነን ተጫውተን የተሻሉ የጎል ሙከራዎች አድርገናል። ከዚ ይበልጥ ብዙ ግቦች ማግባት እንችል ነበር።

ስላባከኗቸው የግብ ዕድሎች

በርካታ ዕድሎች ፈጥረን ያንን ወደ ጎል መቀየር አልቻልንም። በቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይም የግብ ማግባት ችግሮች ነበሩብን። እዛ ላይ ጠንክረን እንሰራለን።



“ስህተቶች ይኖራሉ እነዛን ስህተቶች መታገስ ያስፈልጋል” ካሳዬ አራጌ

ስለ ጨዋታው

ጨዋታው ጥሩ ነበር። ሽረ በተከፈተ ቦታ ላይ ማለትም በመልሶ ማጥቃት ነበር የሚጠቀሙት። እንደዛ አይነት ኳሶች እንዳያገኙ ኳሶቻችን እንዳይባክኑ ያንን ተቆጣጥረን ለመጫወት ነበር የሞከርነው። በመልሶ ማጥቃት ነበር የሚያጠቁት። እነዛን ኳሶች ከኛ እየወሰዱ ነበር የሚጠቀሙት። እነዚህን ስህተቶቻችንን ቀንሰን ግብ ለመፈለግ ነበር የሞከርነው።

ቡድኑ ግብ ማግባት ላይ ስላለው ችግር

በሂደት እያስተካከልን እንሄዳለን። ዛሬም የተወሰኑ ዕድሎች ፈጥረን ነበር፤ ዕድሎች የመጠቀም ክፍተቶች አሉብን። እነዛን ችግሮች እያስተካከልን እንሄዳለን።

የቡድኑ የዚህ ዓመት እቅድ

እቅዳችን አንድ ወጥ የሆነ እና ተጋጣሚ መቋቋም የሚችል ቡድን ማዳበር ነው። ያ በሌለበት ሁኔታ ምናልባት ለግዜው ጨዋታዎችን ማሸነፍ ትችላለህ፤ ግን ዘላቂ ነገር ላይኖረው ይችላል። ዋናው እቅድ በተለይ በዚህ ዓመት በቀጣይ ዓመታት በሂደት ሌሎች ነገሮችም አሉ። በዚ ዓመት ግን አንድ ወጥ የሆነ ስህተቱን በብዙ ረገድ የቀነሰ ቡድን ማዳበር ነው።

ስለ ተጫዋቾቹ ብቃት

ስህተቶች ይኖራሉ፤ እነዛን ስህተቶች መታገስ ያስፈልጋል። ከውጪ የሚመጡት ተጫዋቾች ያንተን ታዳጊ ሊያስተምሩ የሚችሉ መሆን አለባቸው። አለበመዝያ ትርጉም የለውም


© ሶከር ኢትዮጵያ