ከፍተኛ ሊግ | ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሀን በርካታ ተጫዋቾችን አስፈረመ

ሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን አስራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ሀ ላይ የሚገኘው ሰሜን ሸዋ ደብረብርሀን አሰልጣኝ እዮብ ማለን ከለቀቀ በኃላ በምትኩ የቀድሞው የአሰልጣኙ ኃይለየሱስ ጋሻውን መቅጠሩ ይታወሳል፡፡ አሰልጣኙም ለ2013 የከፍተኛ ሊጉ ውድድር ክለቡን ጠንካራ ለማድረግ በማሰብ ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ጨምሮ በድምሩ አስራ ስድስት ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

ግብ ጠባቂ – ሙሴ ገብረኪዳን (ከኢትዮጵያ መድን) እና በለጠ ተስፋዬ

ተከላካዮች – በኃይሉ በለጠ (ከኢኮሥኮ)፣ ልደቱ ጌታቸው (ከኤሌክትሪክ)፣ ዳንኤል አባተ (ከአአ ከተማ)፣ ታምራት በቀለ (ከሞጆ ከተማ)፣ ዮሐንስ ይርሳው (ከሰበታ ከተማ)

አማካዮች – አቤል ዘውዱ (ከአአ ከተማ)፣ ሲሳይ አማረ (ከፌዴራል ፖሊስ)፣ ወንድሜነህ ዘሪሁን (ከሀምበርቾ)፣ ኃይለማርያም እሸቱ (ከደሴ ከተማ)፣ በረከት ከማ (ከአአ ከተማ)

አጥቂዎች- ካሳሁን ሰቦቃ (ከኢትዮጵያ መድን)፣ አትክልት ንጉሤ (ከወሎ ኮምቦልቻ)፣ ሥዩም ደስታ (ከመከላከያ)፣ መሐመድ ዓሊ (ከሻሸመኔ ከተማ)


© ሶከር ኢትዮጵያ