የሴካፋ የምድብ ድልድል ወጥቷል

ዘጠኝ ሀገራት በሚሳተፉበት የሴካፋ ውድድር ላይ የምድብ ድልድሉ ወጥቷል።

ከደቂቃዎች በፊት በበይነ-መረብ በወጣው የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብር ላይ ዘጠኙ ሀገራት በሦስት ምድብ ተደልድለዋል። በዚህም በምድብ 1 ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ዲሞክራቲክ ኮንጎ ሲደለደሉ በምድብ 2 ደግሞ አስተናጋጇ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ እና ኤርትራ ተመድበዋል። በመጨረሻው ምድብ ደግሞ ጂቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ መደልደላቸው ታውቋል።