የከፍተኛ ሊግ የአንደኛ ዙር ግምገማ ቅዳሜ ይከናወናል

የ2014 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የአንደኛው ዙር ግምገማ በያዝነው ሳምንት ቅዳሜ ይደረጋል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር ከሚደረጉ ውድድሮች መካከል አንዱ በሶስት ምድቦች ተከፍሎ በሰላሳ ክለቦች መካከል የሚደረገው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ነው፡፡ ከቀናቶች በፊት የመጀመሪያው ዙር ውድድሮች ተደረገው የተጠናቀቁ ሲሆን የሁለተኛው ዙር ደግሞ የካቲት 12 እንደሚጀመር ፌዴሬሽኑ አስታውቆ ነበር፡፡

ይህ የሁለተኛው ዙር ከመጀመሩ በፊት እንደ ሁልጊዜውም ሁሉ በአንደኛው ዙር የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች እንዲሁም አፈፃፀሙ ምን መልክ ነበረው በማለት ከክለቦች ጋር የሚደረገው የአንደኛው ዙር ግምገማ የፊታችን ቅዳሜ ጥር 21 ልክ 3፡00 ሲል በጁፒተር ሆቴል የክለብ ቡድን መሪዎች እና ውድድሩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እንደሚደረግ ፌዴሬሽኑ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ጠቁሟል፡፡